Saturday, 10 May 2014

ቶርቸር/torture/ ይርጋ የሌለው ወንጀል ነው(ክፍል አንድ)

በቅርቡ ፍርድ ቤት የቀረቡት የዞን ናይን አባላት ፖሊስ የማሰቃየት ተግባር ፈጽሞብናል ብለው ለፍርድ ቤቱ ሲናገሩ ፖሊስ ማስረጃ የላቸውም በማለት ማስተባበሉንና ፍርድ ቤቱም ቶርቸር ህገ መንግስታዊ አይደለም የሚል አስተያየት መስጠቱን ሰምተናል። ዞን ናይኖቹ አቤቱታውን ያቀረቡት ፍርድ ቤቱ መፍት ሄ እንዲሰጣቸው እንጅ በህገ መንግስቱ መከልከሉን ለፖሊስ እንዲያስረዳላቸው እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በ አንደበትማ ከሰለጠንን በጣም ቆየን እኮ። ገና በንጉሱ ዘመን ነው ከ አገር ቀድመን የ አለም አቀፍ የሰ ብ አዊ መብት ድንጋጌ(Universal Declaration on Human Rights) ሲረቀቅና ሲጸድቅ እኛም ነበርንበት። ንጉሱ ህገ መንግስታቸውን ሲከልሱም ከዚሁ ድንጋጌ የወሰዷቸውን አንዳንድ መብቶች ለተገዥዎቻቸው ሰጥተው ነበር። በዚሁ የስልጣኔ መንፈስም ነበር የድሮው የወንጀል ህግ ሲረቀቅ ዘርማጥፋትን የመሳሰሉ የ አለም አቀፍ ወንጀሎች የህጋችን አካል የነበሩት። የሚገርመው ግን ንጉሱን ጥሎ የመጣው ደርግ በቀይ ሽብር ያንን ሁሉ ግፍና ወንጀል ሲፈጽም “ኧረ እንዴት ነው ንጉሱ ያጸደቁት የወንጀል ህግ እንዲህ የሚል አንቀጽ አለው” ያለ አልነበረም። ከነበረም የሰማው የለም። 

አሁንም ዘመናዊ ለመምሰል ህግ ከማውጣት እና ከማጽደቅ፣ ህጉን ሁሉ ችላ ብሎ የፖለቲካ ፉክክሩ ላይ ትኩረት ከማድረግ አልወጣንም። የጊዜው መንግስት ሰዎች ራሳቸውን ከደርግ ጋር እያነጻጸሩ የተሻሉ በመሆናቸው ምስጋና ከመጠበቅ፣ በ አገሪቱ ውስጥ ያሉትን ህጎች ከማክበር አንጻር ያሉበትን ደረጃ እያስተዋሉ እንቅልፍ ቢያጡ ነው የሚሻለው፤ አለበለዚያ በደርግ ሰዎች ላይ የደረሰው በእነሱም ላይ መድረሱ አይቀርም። ምክንያቱም ግልጽ ነው።
የጊዜው ህገ መንግስት ጭካኔ የተሞላበት የማሰቃየት ተግባርን ቀርቶ፣ ኢሰብ አዊ የሆነ ማንኛውንም አያያዝ የሚከለክል ነው። ከዚያም አልፎ ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸው አለም አቀፍ ድንጋጌዎች ሁሉ የህገ መንግስቱ አካል ናቸው የሚል ነው። ያም አልበቃ ብሎ የህገ መንግስቱ ሰ ብ አዊ መብት ነክ አንቀጾች ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው የሰብ አዊ መብት ስምምነቶች መሰረት መተርጎም እንዳለባቸው ያዛል። ይህን ሁሉ እውነት የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንድ ሶስተኛው የሰ ብ አዊ መብት ድንጋጌ ነው ብሎ በከንቱ ለመመጻደቅ ብቻ መጠቀም አይቻልም። ኢትዮጵያ የማሰቃየት ተግባር የሚከለክለው የተባበሩት መንግስታት ጸረ ቶርቸር ስምምነት የፈረመችና ያሰደቀች አገር ናት። ያ ማለት የዚሁ ስምምነት አንቀጾች የ አገሪቱ የህግ አካል ናቸው ማለት ነው።

አለም አቀፍ ህጉን ብንተወው እንኳን አሁን ባለው የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ መሰረት አሰቃይቶ ቃል መቀበል ድርጊቱን የፈጸመውንም ሰው እስከ አስር አመት ድርጊቱን ያዘዘውን ባለስልጣን እስከ አስራ አምስት አመት ሊያሰቀጣ የሚችል ወንጀል ነው። ከጥቂት ቀናት በፊት ለተባበሩት መንግስታት የሰ ብ አዊ መብቶች ጉባ ኤ የኢትዮጵያን የሰ ብ አዊ መብት አያያዝ ሲገመግም የኢትዮጵያ ተወካዮች የ አገሪቱ ስ ር አት ቶርቸርን እንደማይታገስ ገልጸው ነበር። በህግማ በንጉሱ ጊዜ ጀምሮ ሰልጥነናል፤ ልባችን አልሰለጠነም እንጅ። ይህንን ድርጊት የመከላከል ተግባር ከፍተኛ የፖለቲካ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ፣ ተገቢ ተቋማዊና ህጋዊ ማእቀፍ፣ የነቃ ክትትልና የእርማት ስር አት የሚፈልግ ነገር ነው።

ይሄ ሁሉ በ አብዛኛው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሌለ ለማወቅ የኢትዮጵያን እስር ቤቶች ዞሮ መጎብኘት አያስፈልግም። ይሄው በዞን ናይን አባላት፣ በፖሊስ እና በፍርድ ቤት መካከል ተደረገ የተባለው ምልልስ በራሱ ብዙ የሚያስጨብጠን ቁምነገር አለ። አንዳንድ አጠቃላይ ነጥቦችን ላስቀምጥ።

፩ኛ በደርግ ጊዜ ይፈጸም ስለነበረው ኢ ሰብ አዊ የማሰቃየት ተግባር ጉዳቱ የደረሰባቸው ሰዎች ከሚናገሩት፣ በቀይ ሽብር የፍርድ ሂደት ከተገለጡ እውነቶች ብዙ ነገር ተምረናል። ጥቅም ላይ ይውሉ ስለነበሩት የማሰቃያ ቴክኒኮች አዲስ አበባ የሚገኘውን የቀይ ሽብር ሰማእታት ሃውልት መታሰቢያ ጎራ ብሎ በመጎብኘት መረዳት ይቻላል። በዚሁ መታሰቢያ በር ላይ “በፍጹም አይደገምም” የሚል ጽሁፍ ተጽፏል። አሁን ዋናው ጥያቄ በእርግጥ ከዚህ አሰቃቂ ታሪክ ተሻግረን ሄደናል ወይ የሚለው ነው። “አዎ ተሻግረናል፤ አዎ ኢሰብ አዊ የማሰቃየት ተግባር በእስረኞች ላይ አይፈጸምም”፣ ብሎ በእውነትና በድፍረት የሚነግረን ሰው ቢኖር ደስ ባለኝ። እንዳይኖር ስለምንመኝ ብቻ የለም እያልን በእኛም ዘመን እንደዛ ካለው አሰቃቂ ታሪክ መፈጸም ማምለጥ አንችልም።
፪ኛ የሚያስፈልገው መፈክር መደጋገም ሳይሆን እንደዚህ አይነት ተግባር እንዳይፈጸም የሚያስችል የህግ፣ የተቋማትና የ አሰራር ስር አት መዘርጋት ነው። ያ እስካልተፈጸመ ድረስ ማንም በመንግስት ሃላፊነት ላይ ያለ ሰው ራሱ በቀጥታ ስላላደረገው ብቻ ከእንደዚህ አይነቱ ነውረኛ ወንጀል ተጠያቂነት አያመልጥም። ሰ ብ አዊ መብት የሚባል ጽንሰ ሃሳብ በማይታወቅበት ዘመን ሚኒሊክ እንዲህ ወይም እንዲያ ያለውን ወንጀል ፈጽሟል እያልን ስንመጻደቅ የምንውል ሰዎች ራሳችን እያጨበጨብን ያጸደቅነውን ህገ መንግስትና ሌሎች ህጎች በ አሳፋሪ መንገድ ችላ ብንለው ከታሪክ እና ከፖለቲካ ተጠያቂነት ባሻገር ከህግ ተጠያቂነትም አናመልጥም።

የሚገርመው ነገር የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ራሱ በአንቀጽ ሃያ ስምንት ላይ በስብዕና ላይ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲደነግግ ከሌሎች አለም አቀፍ ወንጀሎች ባሻገር፣ ቶርቸር ወይም ኢ ሰብዐዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም ይለናል። ያ ማለት የዛሬ አምሳ እና ስድሳ አመት ራሱ ዛሬ በየትኛውም የኢትዮጵያ እስርቤት ሰዎችን በ አሰቃቂ ሁኔታ የሚያሰቃዩ ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው እየተነጠቁ ወደ እስር ቤት ይላካሉ። ደርግ የ ሃይለ ስላሴን የወንጀል ህግ ችላ ብሎ በሰራው ወንጀል ከቅጣት እንዳላመለጠ፣ የጊዜው መንግስት ሰዎችም “ለህገ መንግስታዊ ስ ር አቱ መከበር በሚል” ሰበብ ለሚሰሩት ጸያፍ ተግባር ከተጠያቂነት አያመልጡም።

No comments:

Post a Comment