Friday, 30 November 2012

Taking the FDRE constitution and its human rights provisions seriously



Writing at a time when there was a lot of confusion about the health of PM Meles, I wrote the following:  -What I found really depressing about our reaction to the situation is to know that how little trust we have in our Constitution and in the system it created. A parliament of more than five hundred representatives feels helpless when the Prime Minister is sick. People make little reference for the Constitutional provisions which might have implication in these circumstances. People don’t talk about the fact that our Constitution is surprisingly silent as to what should happen when the PM gets sick. Even lawyers don’t talk about what it means when the Constitution says the Dupty Prime Minister acts on behalf of the Prime Minister in his absence. 

I generally like arguments based on (un)constitutionality. In a blog post I never posted which I wrote approximately four months ago, I argued that taking our constitution and its human rights provisions seriously might be a very good solution for most of our problems. My argument goes like this: The Ethiopian constitution has a very long list of human rights which in principle should be interpreted based on international standards. Parliamentarians, judges, prosecutors, teachers, journalists, and any person who has some kind of responsibility in the country should take the Constitution very seriously. We should keep thinking, talking, teaching and writing about it. We should keep supporting our arguments based on its provisions. The more we do these things in a convincing manner, the lesser the chance will be for the government to rely on unconvincing arguments and silly legal manipulations to justify its acts.

Let me mention some examples which I then called “encouraging signs at depressing times”. (Though they are my own words, I will put them in quotation.)  
"Few months ago, there was a lot of talk about forced displacement of some Ethiopian citizens from one part of the country to another part of the country. It was depressing news for many people. However, there were some encouraging signs at the same time. The discussion basically revolved around the rights of those citizens to reside in any part of the country. The advantage with these kinds of arguments which are based on human rights is that they will substantially limit the possible arguments of the other party, in this case, the government. At least the government didn’t and couldn’t dare to say it is ok to displace people. It at least contested the numbers and tried to justify its action.

Another example was the discussion that followed after the Prime Minister(Meles) was challenged in the Parliament on the basis that some programmes which were being transmitted on ETV were against presumption of innocence of the accused persons. The Prime Minister wrongly answered the question claiming “presumption of innocence of the government”. Given the public discussion that followed, perhaps the legal advisors of the PM might have told him that, because of the Constitution the arguments he can make are not unlimited.”(NB: this was drafted before the death of Meles)

I can also mention more examples. When the news about Andualem Arage being attacked in prison by a convicted prisoner came out, the right of accused persons not to be imprisoned together with convicted prisoners was found to be a very important argument against which the government could not bring a legally acceptable counter argument.   I found the role such arguments/possible arguments based on the Constitution and human rights in shaping public discussions and limiting possible arguments very encouraging.

Despite the encouraging efforts in using constitutional rights and provisions to support arguments in our discussions, what is still a problem is the fact that the Courts(especially those entertaining anti-terrorism charges)  do not seem to be much influenced by such kinds of arguments. We recently heard that the advocates for the Muslim leaders who are accused of terrorism raised a challenge of constitutionality in the High court. That is encouraging too.(at this point some people will laugh at me saying it is the task of the HoF to interpret the Constitution. ) But I still think people should keep making well-articulated arguments based on the human rights provisions of the Constitution in Ethiopian courts to the extent that it would be impossible to ignore them.

I am not claiming that talking about them will go a long way in ensuring their enforcement. However, we should also understand the power legal, constitutional and human rights arguments have in shaping discussions and ultimately affecting behaviour.  After all, nobody is looking for a flawless system. We are rather looking for a system which can correct its mistakes, a system which can respond fast when problems occur and a system which can properly work. I believe the government, the opposition, and the general public should give attention to the constitutional provisions and their enforcement. 

What generally frustrates me the most is not the fact that we are not currently doing well in terms of human rights and in terms of building a more democratic system. What frustrates me the most is to know that we have uncertain future. What frustrates me the most is to know that our fate as a country is more dependent on a party called EPRDF than a constitution which we have lived with for about 17 years. Don’t think that the uncertainty is in my imagination. I think in the few months following the sickness and the death of PM Meles, that uncertainty was also clear to those who are now in power.  Some people might think this frustration is a result of a hidden desire to impose my own image of what Ethiopia should be like on others. No! It is not. That is exactly why I like arguments based on the FDRE Constitution. That is a document which was written and introduced by the current government. The government has the duty to adhere to it. The commitment of the government to defend the Constitution should not be limited to those parts of the Constitution which the government found favorable to its own agenda. Can we please keep talking about the Constitution with a hope that those discussions will affect the actions of the government in the future? You think that is not worth talking? You might be right. But, as you know, most of us are silent any way. And something is better than nothing. 

Tuesday, 27 November 2012

መረዳት መርዳት ነው።


  • መረዳት መርዳት ነው።


ይህ አረፍተ ነገር ሁለት ትርጉም ነው ያለው። አንዱ የሌሎችን እርዳታ መቀበል በራሱ መርዳት ነው የሚል ሲሆን ሌላው ደግሞ ሌሎችን ሰዎች መረዳት(understand) ማድረግ እርዳታ እንደማድረግ ነው የሚል ትርጉም አለው። ብዙ ጊዜ ይህን አገላለጽ እጠቀመዋለሁ። የምጠቀመው ግን በሁለተኛው ትርጉሙ ነው። በእርግጥ በመጀመሪያ ትርጉሙም ስሜት እንዲሰጥ ሊደርግ ይችል ይሆናል። ማን ያውቃል? የተቸገረ የምታበላው፣ የተጠማ የምታጠጣው ለራስህ ጽድቅ እስከሆነ ድረስ ችግረኛው በመቸገሩ አንተ ራስህን የምትገልጽበት እና ጽድቅን የምታገኝበት መንገድ ስለፈጠረልህ እየረዳህ ነው የሚል ክርክር የሚያቀርብ ሰው አይጠፋም።

እኔ ግን መጠቀም የምፈልገው በሁለተኛው ትርጉሙ ነው። በእውነቱ ብዙ ጊዜ እንነጋገራለን እንጅ አንረዳዳም። አንዳችን አንዳችንን ባለመረዳታችንም የተነሳ፣ በመረዳዳት  understand በመደራረግ ልናገኘው እንችል የነበረውን እረፍት ራሳችንን እንነፍጋለን። በቸገረህ ጊዜ ችግርህን የማያቃልልህ ቢሆን እንኳ ችግርህን የሚረዳህ ሰው ማግኘት ምንኛ መልካም ነገር ነው። በጨነቀሽ ጊዜ ጭንቀትሽን ችሎ የሚያቀል ሰው ባይገኝ እንኳ የሚረዳ ሰው ማግኘት ምንኛ መልካም ነው። አዎ መረዳት መርዳት ነው።

እንግዲህ መረዳት መርዳት ከሆነ አለመረዳት መጉዳት ነው ሊባልም ይችላል። ነገር ግን ነገሩ በ ሉታዊ እና በወቀሳ መንገድ ከሚቀርብ ይልቅ በ አወንታዊ መንገድ ቢቀርብ የተሻለ ነው። ከዚህ ጋር አያይዤ አንድ ዛሬ በ አእምሮዬ እየተመላለሰ ስላለ ሃሳብ ልግለጽ። በመረዳት እርዱኝ።

በሁለት ሰዎች መካከል ያለ ርቀት በሁለት ነጥቦች መካከል እንዳለ እርቀት አይደለም። በሁለት ሰዎች መካከል ያለው ርቀት ርቀቱን መለካት ከምትጀምርበት አቅጣጫ ይወሰናል- ነው የሚለው ሃሳቡ። ፌስ ቡክ ላይ ለጥፌዋለሁ(The distance between two persons is not like the distance between two points. In case of persons, the distance depends on which side you start to measure) በመረዳት  የረዱኝ ሰዎች እንደሚኖሩ እገምታለሁ። ለማለት የፈለኩት እንዲህ ነው። በሁለት ነጥቦች መካከል ያለ ርቀት ሲባል፣ አካላዊ ርቀትን የሚወክል ነው። ወረቀት ላይ ሁለት ነጥቦች ምልክት አድርገህ ከየትኛውም ነጥብ ተነስተህ ብትለካ ርቀቱ ያው ነው። በሰዎች መካከል ያለ ርቀት ስል ግን የቅርበት፣ የጓደኝነት፣ የፍቅር፣ የመተሳሳሰብ ርቀት ማለቴ ነው። እሱ እንደ ወንድም የሚያይህን ሰው፣ አንተ እንደ ሩቅ ሰው የምታየው ከሆነ በመካከላች ሁ ያለው ርቀት ካንተ ተጀምሮ ሲለካ ረጅም ሲሆን፣ ከሱ ተጀምሮ ሲለካ ግን በጣም አጭር ነው። ያመንኩት ከዳኝ ብሎ ሰው የሚያማርረው፣ ለልቡ ቅርብ የሆነን ሰው፣ በመካከላቸው ያለው ርቀት ከሌላኛው ወገን ተጀምሮ ሲለካ የገዘፈ መሆኑን ሳይረዳ በመቆየት ነው። ክንፍህን ዘርግተህ/ሽ  በደበበ ሰይፉ አገላለጽ "አበባ አሳብበህ/ሽ አዱኛ ሰብስበህ/ሽ የጠበቅከው/ሽው ሰው   የማይከሰትበት ምክንያት ይህ ሊሆን ይችላል። ባልተጠበቀ ሁኔታ በቅንነት የምታስበው ሰው ኩርፊያ የሚያውጅብህ ሳታውቀው በመካከላችሁ ያለው ርቀት ከሱ ተነስቶ ሲለካ በጣም ገዝፎ ሊሆን ይችላል።

 ይህ ነገር የበለጠ በመረዳዳት እና እራስን በማስረዳት ሊቀረፍ ይችል ይሆናል። በእርግጠኝነት ግን መናገር አልችልም። ታዲያ በኔ ግምት ግድ አለን ለምንላችው መስተጋብሮች ርቀቱን እኩል ማድረግ ባይችል እንኳን ተቀራራቢ ማድረግ መልካም ነው። ለዚህም መረዳዳት ሳይረዳ አይቀርም። ሌሎችን ሰዎች በመረዳት እንርዳቸው። ሃሳቡን ያቀረብኩት ለራሴም ነው። በመርዳት እንርዳ፣ ፋይዳ ያላቸው ርቀቶቻችንን እናቀራርብ።

Tuesday, 25 September 2012

በግጥም ስንተክዝ


የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ የጻፍኳቸውን ግጥሞች መለስ ብዬ በመርመር ላይ እገኛለሁ። ጥቂት ያንድ ሰሞን ግጥሞችን ሳልበርዝ እንደተጻፉ ላካፍላቻሁ ወደድኩ። 

      ከጊዜ ውቅያኖስ
ባጭር ጭልፋ ጨልፎ ያችኑ አፍስሶ፣
                             እሷን ተንተርሶ፣
ነጥብ ታክል ነገር ታፋፋኝ ታኩራራኝ
                        ታሳድገኝ ብሎ፣
ትልቅ በመሰለው ሰው በጊዜው አድሮ፣ ሰው በጊዜው ውሎ
                                         ሰው በጊዜው ኑሮ
ምነዋ ባልሆነ የንፋሱ ሲሳይ ግልብ እንደገለባ፣
በስሜቱ ፍላት ገደል የሚገባ።
ከጊዜ ውቅያኖስ በጭልፋ ተጨልፎ
                    በዚያች ተነክሮ
እየረዘመበት ቀንና ሌሊቱ  ማታና  መአልቱ
እየተቸገረ እራሱ ኢምንቱ ለኢምንት ኢምንቱ
                                 ላጉል እሱነቱ
ተላላው ወንድሜ እኔ እኔ ያበዛል
ይውም ከኔነቱ ይሁን ላለው ጥቅሙ
                  ለምናብ አለሙ።
                       11-10-92 E.C.

****************************

“ያበደ” አላበደም
“ያበደ” አላበደም
“ያላበድን” አብደናል፣
“ጤነኞች”  የሆንን እውነቱ ጠፍቶናል፣
ፍቅር እንደ መጥፎ ያቅለሸልሸናል፣
መቻቻል እንደ ሬት ያንገፈግፈናል።
እኛ በራሳችን ብዙ ግፍ ሰርተናል፣
እየተገላለጥን እራቁት ሆነናል፣
እየተገፋፋን ተንጋለን አልቀናል፣
“ያበደ”  አላበደምያላበድን” አብደናል።

አለም በቃኝ ብሎ ብልህ ይመንናል፣
እብደት በቃኝ ብሎእብድ” ልብስ ያወልቃል፣
                           መርሳትን ያጠልቃል፣
እሱ ትክክል ነውያበደ” መች አብዷል
እኛ ግን ቀውሰን ፍቅርን አውልቀናል፣
ጤነኛ ነን ባዮችያላበድን” አብደናል።
17-10-92

**************************

ለ'ንቅልፍ ለ'ንቅልፍማ
ብርሃን ወገጋን ጨረር ተርከፍክፎ፣
ሁሉ ጎልቶ ሲታይ ጸዳል ተነጣጥፎ፣
                   አይንን ካልገለጡ፣
በብርሃን ፋና ለስራ ካልወጡ፣
በእውቀት በልጽገው ምንድንም ካልሰጡ፣
የማይበሩ ሻሞች ሆነው ከቀለጡ፣
ለንቅልፍ ለንቅልፍማ ጨለማን ማን በልጦ፣
የጸጥታው ድባብ ከሱ መቼ ታጥቶ፣
ለንቅልፍ ለንቅልፍማ ለወሬ ለቅዠት፣
ጨለማ ይሻላል ቁርጡን የለየለት፣
ቢገልጡም ቢከድኑም ለውጥ የማይኖርበት።
17-10-92

**********************

የበሰለ ተስፋ
የሮጠው እግር የሮጠው፣
ሩጫውንም ባይጠግበው፣
ሩጫው ግን በቃው ጠገበው፣
             እድሜ ገደበው።
የፈሰሰው ተስፋ ተስፋው፣
ሩቅ መስሎ ከቅርብ ያለው፣
ግድቡን ደርሶ ተመልሶ፣
ት ዝታ ብቻ ቀረው።
በዚህ ዛሬ
ቆዳ ሳይናደድ ሲኮሳተር፣
ወገብ ሲሰግድ ወደምድር፣
አይነ ስጋ ሲደክም
የት ዝታ ምጣድ ሲግም፣
ስራውን አበጥሮ
ተግባሩን ጋግሮ
የተጋገረው ት ዝታ
በዚህ ማታ
ከ’ድሜ ገበታ
ት ዝታ ብቻ ሳይሆን ተስፋም ነው፣
                  የበሰለ ተስፋ፣
የሞት ድልድይን ላለመፍራት፣
                መንፈስን የሚያፋፋ።
                               20-10-92 E.C. 

Thursday, 13 September 2012

ይቅርታ ይደረግልኝና



ከጥቂት ወራት በፊት አንድ ስዊድናዊ ተማሪ ስትፈራ ስትቸር ስለ አገራችን የፍትህ ስርአት እና የዳኞች ብቃት አንዳንድ ጥያቄዎች አነሳችልኝ። ይህ የሆነው ያገራችን አንድ የከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለት ስዊድናዊ ጋዜጠኞች ላይ የአስራ አንድ የአስራ አንድ አመት ቅጣት እንደወሰነ ሰሞን ነው። ለመገንዘብ ያዳገታት ነገር ቢኖር ተገቢ የህግ ትምህርት የተከታተለ ሰው እንዴት በህገ ወጥ መንገድም ቢሆን ለመዋጋት ሳይሆን ለመዘገብ ወደ ሌላ አገር የገቡ ሰዎችን በሽብርተኝነት እንደሚቀጣ ነው። ነገሩን ለማስረዳት የማደርገው ጥረት የባሰ የአገራችንን እውነታ እያወሳሰበባት ሲሄድ ይህ ነገር በነሱ ላይ የተጀመረ አለመሆኑን እና ሽብርተኛ ተብሎ ከተሰየመ ድርጅት ጋር በህገ ወጥ መንገድ ለዘጋቢዎች በተከለከለ አካባቢ በመገኘታቸው፣ መሃል አዲስ አበባ ተቀምጠው በሚጽፉት ጽሁፍ ተመሳሳይ ክስ ከሚመሰረትባቸው ያገሬ ሰዎች አንጻር የነሱ መከሰስም ሆነ ፍርዱ እንደማይገርመኝ ገልጬ፣ ይቅርታ ከጠየቁ ግን ሊፈቱ እንደሚችሉ በትህትና አስረዳሁ።

አሁን በይቅርታ ሲፈቱ ስለ እውነታው መለስ ብሎ ለማሰብ እድል አገኘሁ፤ በነዚህ ሁለት ሲውድናውያን ክስ ጉዳይ ብዙዎች ሲያዝኑና ሲተክዙ ተመልክቻለሁ፤ ተገቢ ሊሆን ይችላል። እነዚህ ሰዎች ግን ወንጀል መፈጸማቸው ለማንም የተሰወረ አይደለም፤ በእርግጥ ወንጀሉ "ሽብርተኝነት"፣ ወይም "ሽብርተኘነትን መደገፍ" የሚለው ስም ሊበዛበት ይችላል። ወንጀል መሆኑን ለማወቅ የሄዱበት አውሮፓ የ አፍርካን ስደተኞች ምን እንደሚያደርግ መመልከት ይበቃል። የሚገርመው ነገር እነዚህ ሰዎች እንደ ስደተኛ አፍሪካውያን እንኳን እራሳቸውን ከችግር ለማዳን አይደለም ወደ እዚያ ያመሩት። ለመሄድ ሲወስኑ ራሳቸውን ችግር ውስጥ እየከተቱ መሆኑንም ቢሆን ጠንቅቀው ያውቁታል። በተያዙበት ቦታ እና ሁነታ ከዚህ የባሰ አደጋ ያላጋጠማቸው መሆኑ በእርግጥ እድለኞች ነበሩ የሚያስብል ነው፤ ይቅርታ ይደረግልኝና እኔ ከነሱ ይልቅ በጣም የሚከነክነኝ፣ በስደት ተቀምጠው ጻፉ ተብለው የተፈረደባቸው ወገኖቼ ናቸው፤ ይቅርታ ይደረግልኝና እኔን የሚከነክነኝ ምንም ይሁን በጻፉት እና በተናገሩት መነሻ ለእስር እና ለቅጣት የተዳረጉ፣ ምናልባትም ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ያላት አገር እስክትሆን ድረስ በእስር ሊቆዩ የሚችሉ ያገሬ ሰዎች መኖራቸውን መረዳት ነው፤ ህግ ከለጠጡት የማይደርስበት ቦታ አለመኖሩን ስለሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎች ተመሳሳይ አስተሳሰብ እና አመለካከት ያላቸውን ሰዎች የማሸማቀቅ እድሉ የሰፋ በመሆኑ ያሳዝነኛል፤ ብዙ ሰዎች ስለ ሌሎች ሰዎች የመናገር እና የመጻፍ መብት መጨነቅ ያለብህ እነዚሁ ሰዎች በሚጽፉት እና በሚናገሩት ስትስማማ ብቻ ይመስላቸዋል። ይህ የተሳሳተ አመለካከት ይመስለኛል፤ በሃሳቡ አለመስማማት አንድ ነገር ነው፤ በማትስማማበት ሃሳብ እና በወንጀል መካከል ግን ሰፊ ልዩነት አለ። አሁን በቅርብ አንድ የኢሳት ጋዜጠኛ አንድ የሻብያ የፕሮፓጋንዳ ባለሙያ ጋብዞ ስለ ኤርትራ ዲሞክራሲ እና ነጻ ፕሬስ ስብከት ሲያሰጠን፣ መለስን ከኢሳያስ ጋር ለማቀራረብ ጥረት ሲያደርግ በጣም አበሳጭቶኛል፤ ታዲያ ይህ ሰው ከጠላት ጋር በመተባበር ባገር ክህደት ተከሶ ቢፈረድበት ሃሳቡን አምርሬ ስለጠላሁት ፍርዱን እቀበላለሁ ማለት ነው? እንደዚህ መሆን የለበትም።

የማትፈልገውን እና የማይጥምህን ሃሳብ ዝም የማሰኘት ጽኑ ፍላጎት የአምባገነንት ዋና ምልክት ነው፤ ይህ አዝማሚያ በሁሉም ሰው ላይ አለ። በመንግስት ላይ በኖረ ጊዜ አደጋው ከፍ ይላል። "የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ" ልጆች ይህን ጽኑ ፍላጎታቸውን የሚወጡት ጠላቶቻችን የሚሏቸውን በመግደል ለዘላለም ዝም በማሰኘት ነበር። አሁን መሻሻል ቢኖርም አቅመ ቢስ ድምጾችን ሳይቀር የማፈን ጽኑ ፍላጎት መኖሩ ለማንም የተሰወረ አይደለም። 

እስክንድር ነጋ እና ሌሎች በእስር ያሉ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ መፈለግ ያለብን ጻፉት ወይም አሉት ከሚባለው ነገር ጋር ከተስማማን ብቻ መሆን የለበትም፤ በተናገረው ወይም በጻፈው መስማማት አለመስማማት አንድ ነገር ነው፤ የ አስራ ስምንት አመት እስራት ሲፈረድበት ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ እና ምንም ነገር እንዳልሆነ ብሎም ጉዳዩ የህግ የበላይነት ጉዳይ ብቻ እንደሆነ አድርጎ መከራከር ያስተዛዝባል። በእርግጥ መንግስት እና ሌሎች ያገሪቱ የፖለቲካ ሃይሎች የህግ ሁኔታውን እንዳወሳሰቡት ለማንም የተሰወረ አይደለም፤ ጥቂት የማይባሉ በሁሉም መንገድ እንታገላለን የሚሉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች በአንድ በኩል፣ መንግስት ደግሞ በሌላ ወገን ሆነው ሰላማዊ እና ህገመንግስታዊ ሊባል የሚችለውን እንቅስቃሴ ማጣበባቸው እሙን ነው። በሁሉም መንገድ እንታገላለን የሚሉቱ መፍትሄውን ከ ህግ ውጭ በመፈለግ፣ መንግስት ደግሞ ከህግ ውጭ በው ይይት፣ በድርድር፣ ገፍተው ሲመጡ ደግሞ በፍልሚያ ሊያገኝ የሚገባውን መፍት ሄ ከህግ ለማግኘት በመሞከር ህገ መንግስታዊ ስር አቱን በግልጽና በስውር ይፈታተኑታል። የሁለቱም አሰላለፍ ባጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት የተቀያየረ በመሆኑ የተመልካቹን የህዝብን አስተሳሰብ በከፍተኛው ያናውጣል። 

ይህ ሰላማዊ እና ህገመንግስታዊ መንገድ በተጣበበ ቁጥር ሰዎችን በራሳቸው አእምሮ ውስጥ የቅድመ ምርመራ መሳሪያ አስገጥመው መንቀሳቀስ ይጀምራሉ፤ ማሰብ ባያቆሙም፣ ያሰቡትን መናገር ያቆማሉ፤ መታዘብ ባያቆሙም፣ ይታዘቡትን መናገር ያቆማሉ። ታዲያ በዚህ የተነሳ ጋዜጠኞች በጻፉ ቁጥር በመብታቸው እየተጠቀሙ ይሁን ወንጀል እየፈጸሙ ለማወቅ አይችሉም። በዚህ የተነሳ በሚፈጠረው ድባብ የሚሰማህን በጻፍክ ጊዜ ሰዎች "ፖለቲከኛ መሆን ፈለክ እንዴ?" "መታሰር ፈለክ እንዴ?" 'ሽብርተኛ መሆን ፈለክ እንዴ?" እያሉ በቀልድም ቢሆን የሚያጥረንን የነጻነት አየር እውነት እንድትጋፈጥ ያደርጉሃል። ለዚህ የነጻነት አየር ሲባል ጋዜጠኞች እና ሃሳባቸውን በመግለጽ ራሳቸውን የሚገድቡ ፖለቲከኞች በሽብርተኝነት ሲከሰሱ እና ሲታሰሩ ሃሳባቸውን እና የፖለቲካ አቋማቸውን ደገፍነውም አልደገፍነውም ሊከነክነን ይገባል።

ይህ የነጻነት አየር ከህገ መንግስቱ የሚመነጭ ነው፤ በዚህ ነጻነት አየር ላይ የሚጨመር የጥርጣሬ እና የፍርሃት ጭስ ህገመንግስታዊ ስር አቱን ቀስ በቀስ የሚሸረሽር መጥፎ አዝማሚያ ነው። "የኢትዮጵያን ህገመንግስታዊ ስርአት በጸና መሰረት ላይ ማቆም" ከፈለግን ለሁሉም አንቀጾቹ እኩል ተቆርቋሪነት ልናሳይ ይገባል።

በእኔ እምነት በመለስ ስርአት ውስጥ ከተበረከቱልን መልካም ነገሮች መካከል በኢትዮጵያ ህገ መንግስት ውስጥ የተካተቱ የሰብ አዊ መብቶች ዝርዝር አንዱ ነው፤ ወደ እርግጠኝነት በተቃረበ ስሜት ማለት የምችለው ነገር ቢኖር፣ ኢህአዴግ አሁን የኢትዮጵያን ህገ መንግስት እንደገና ለመጻፍ እድል ቢሰጠው በተመሳሳይ መንገድ መብቶችን ይዘረዝራል ብዬ አላስብም፤ በተለይም፣ የመብቶችን አተረጓጎም በ አለም አቀፍ የ ሰብ አዊ መብት ሰነዶች መሰረት መሆን አለበት ይላል ብዬ አልጠብቅም። እንደማስበው ከሆነ ይህ ህገመንግስታዊ አቀራረብ፣ የኢትዮጵያን ዳኞች በህገ መንግስቱ ውስጥ የተካተቱ መብቶችን በ አለም አቀፍ ደረጃ ባላቸው ትር ጓሜ መሰረት እንዲተረጉሙ እድሉን ይሰጣቸዋል። ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የሚያጣብቡ የወንጀል ክሶች በተነሱ ቁጥር ዳኞቹ በወንጀል ህጉ አንቀጽ ላይ ብቻ ትኩረት የሚያደርጉ ከሆነ ፍርድ ቤቶች ከአስፈጻሚው አካል ነጻ ቢሆኑ እንኳን ነጻ መልቀቁ ቀርቶ ከባድ ቅጣት ከመወሰን ወደ ኋላ አይሉም። እስካሁን እያየነው ያለነው ይህንኑ ይመስላል።

አንዳንድ ሰዎች "ፍርድቤት ነጻ አይደለም ባስፈጻሚው ቁጥጥር ውስጥ ነው" ብዬ ለመናገር የማልደፍርበት ምክንያት ሊገርማቸው ይችላል። ምክንያቴ ግን ግልጽ ነው፤ የእስክንድር ነጋን ክስ የመረመረው ዳኛ ውሳኔውን የሰጠው የቀረበለትን ማስረጃ መርምሮ ይሁን ከአስፈጻሚው ትእዛዝ ተቀብሎ እራሱ ያውቃል።(ይህን ያነበቡ አንዳንድ ሰዎች "አሃ አንተ የፍርድ ቤት ነጻነትን ትእዛዝ በመቀበል እና ባለመቀበል ነው ማለት ነው የምትተረጉመው?" ሊሉኝ ይችላሉ።አይደለም!)  ትእዛዝ ሳይቀበል በመሰለው እየሰራ ቢሆንና እኔ በሽህዎች ኪሎሜትሮች ርቄ ተቀምጨ ትእዛዝ እንደሚቀበል እርግጠኛ ብሆን ማን ነው የተሳሳተው? ይህንን የማደርገው የተከሰሰበትን አንቀጽ ፣ የቀረበበትን ማስረጃ፣ ያቀረበውን መከላከያ ሳላይ ለማወቅም ሳልፈልግ ከሆነ እንዴት አድርጌ ትክክል መሆን እችላለሁ? እንደዛ የማደርግ ከሆነማ የተከሰሰበትን አንቀጽ፣ የቀረበበትን ማስረጃ፣ ያቀረበውን መከላከያ ቢያውቁም ባያውቁም፣ ውሳኔው በህገ መንግስቱ ውስጥ የተካተተውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይጥሳል ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ቢያውቁም ባያውቁም፣ የሚወዱት እና የሚደግፉት መንግስት የሚደግፈው ውሳኔ ስለሆነ ብቻ እስክንድር ነጋ ለ አስራ ስምንት አመታት በእስር ቤት ውስጥ በመቆየት "ለማህበረሰብ ጎጂ የሆነው ጸባዩ ታርሞ"፣ "ለህብረተሰብ እንደገና ጠቃሚ ሰው" ሆኖ መውጣት አለበት የሚሉትን ሰዎች መምሰሌ ነው። ለዛም ነው አብዛኛው ክርክር በህገመንግስት መብቶች መከበር እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ዙሪያ እንዲሆን የምፈልገው።  ለዛም ነው ሃሳብን በነጻነት ከመግለጽ ጋር የመጻረር ባህሪ ያላቸው የወንጀል ክሶችን የሚያዩ ዳኞች አይናቸውን ጨፍነው ውሳኔ የሚሰጡ ናቸው ብዬ ለመከራከር የሚከብደኝ።

አንድ ቀን መንግስት እርግጠኛ ሆኖ ወደ ፍርድ ቤት የወሰደው የሽብርተኝነት ክስ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በጥልቅ የህግ ትንታኔ ውድቅ ያደረገ ጊዜ፣ ከማንም የማያንስ ህጋችን ከማንም በማያንስ መንገድ በተተረጎመ ጊዜ፣ ያኔ በፍርድ ቤቶች ላይ ያለን እምነት ከፍ ይላል። በፍርድ ቤቶቻችን ላይ ያለን እምነት ከፍ ባለ ጊዜ፣ ህግን እና ህግን ብቻ መሰረት አድርገው እንደሚወስኑ ባወቅን ጊዜ፣ በፍርድ ቤት የተፈረደበትን ሰው "ጋዜጠኛ እኮ ነው"፤ "መብቱን እኮ ነው የተጠቀመው" ብለን የምንጮኸውን ጭሆት እንቀንሳለን። አሁን ግን እዚያ ጊዜ ላይ አይደለንም፤ የክስም የይቅርታም አጠቃቀም በፍትህ ስርአታችን ሙሉ እምነት እንዲኖረን አያደርገንም። 

ከሁሉም ቀላል የሆነው መንገድ ግን ቆይተን  ትዝብት ላይ ከምንወድቅ፣ እነዚህ አይነት ክሶችን አስቀድሞ አለመጀመር ነው፤ በእርግጥ ይቅርታም ቢሆን ይወጣል ብለን ካልጠበቅንበት ማጥ ውስጥ አውጥቶ አማረም ከፋም እንደገና ደህና እንድንመስል ያደረገን መልካም ነገር በመሆኑ እወደዋለሁ፤ በድህረ ዘጠና ሰባት የተቃዋሚ ፖለቲከኞች እስራት ጊዜ ከጓደኞቼ ጋር ሳወራ በተመሰረተባቸው ክስ ምክንያት ሞት ሊፈረድባቸው እንደሚችል ሲጠቁመኝ የተሰማኝ ስሜት እና የሰጠሁት አስተያየት እስካሁን አይረሳኝም። "ያ የሚሆን ከሆነ ኢትዮጵያ አገሬ አይደለችም፤"ነበር ያልኩት በከፍተኛ ብስጭት እና ስሜት።  የሆነውን ሁላችንም እናውቃለን፤ ሚሊኒየም ከመከበሩ በፊት የታሰሩት ሰዎች በይቅርታ ሲፈቱ መጀመሪያም መታሰር አልነበረባቸውም ብሎ የሚያምንም ሰው ቢሆን ደስ ተሰኝቷል፤

ከዚያ በኋላ በግለሰብ ደረጃ ሌላ ህግ ተኮር ብስጭት የደረሰብኝ የ ብርቱካን ሚዴቅሳ ይቅርታ ተነስቶ ወደ እስር ቤት ስትመለስ ነው፤ እስከ አሁንም ድረስ ሳስበው እውነት አይመስለኝም፤ "ሌላ አገር ሄደሽ ይቅርታ አልጠየኩም ብለሽ ስለተናገርሽ  ያገኘሽው ይቅርታ ተጭበርብሮ የተገኘ ስለሆነ፣ ይህም በኢትዮጵያ ህግ መሰረት ዋጋ ስለሌለው ተመልሰሽ ወደ እስር ቤት ትገቢያለሽ" ነበር የመንግስት ክርክር፤ ይቅርታ አድርጉልኝና ይህንን ክርክር በህይወቴ ከሰማኋቸው አስቂኝ እና እጅግ አበሳጭ የህግ ክርክሮች እንደ አንዱ አድርጌ እቆጥረዋለሁ።  ለምን ያላችሁኝ እንደሆነ ስዊድን አገር ሄዳ ተናገረችው የተባለ ነገርን የሰማ መንግስት አዲስ ነገር ላይ የጻፈችውን ደብዳቤ ማንበብ አልቻለም። ያም ሆኖ ይቅርታን እወደዋለሁ፤ በስህተት ተመልሳ ታስራ በይቅርታ ስትፈታም ብዙዎቻችን ደስ ብሎናል።

በቅርቡ ደግሞ ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች ይቅርታ ጠይቀው ሲፈቱ እንደ መልካም ነገር ተቀብለነዋል። ያም ቢሆን ግን ከነሱ ይልቅ የሚያሳስቡን ነገሮች አሉ፤ ምንም እንኳን የእስክንድር ነጋን ክስ እና የክስ ሂደት በቅርበት ባልከታተልም፣ በ አብይ እና በመስፍን ላይ ከተወሰነው የስምንት አመት ፍርድ አንጻር ስመለከተው (አድርገውታል የሚባለውን ነገር ስለምረዳ) መብትን ከመጠቀም አልፎ ለዚህ ቅጣት የሚያበቃ ከባድ ወንጀል ተደርጎ መወሰድ ያለበት ስራ ሰርቷል ብዬ አላምንም። ከሁሉም በላይ ደግሞ እሱና መሰሎቹ ለህብረተሰብ ጎጅ ሆነው በመወሰድ በማረሚያ ቤት ውስጥ ላያሌ አመታት መቀመጥ የለባቸውም። ይህ ታሪክን የማበላሸት ተግባር ነው፤ አብሮህ ዘመን የሚጋራን ሰው በግድ ዝም ማሰኘት ልትችል ትችላለህ፤ ነገር ግን ከህሌናው ሚዛን አታመልጥም፤ ከታሪክ ተወቃሽነትም አትድንም። ይህን ጽሁፍ የጻፍኩት እስክንድር ነጋ እና መሰሎቹ ተፈትተው እንደኛ የነጻነትን አየር እየተነፈሱ በሚጽፉት ጽሁፍ እና በሚያቀርቡት ሃሳብ የሚፈልግ እንዲወዳቸው፣ የሚፈልግ እንዲያጥላላቸው እድል የሚያገኙበትን ቀን እየናፈቅኩ ነው።  

Friday, 17 August 2012

ምናባዊ ክርክር


ይልቁንም ያይኔን እውነት፣ ለልቤ ያጫወትኩት ቢመስለኝ
ለራሴ የጻፍኩትን ደብዳቤ፣ ላንተ መላኩ አሰኘኝ።
                                                               ለራስ የተጻፈ ደብዳቤ, ደበበ ሰይፉ, 1966
ምናባዊ ክርክር
ዲሞክራሲ ተኳኩላ ወደ ኢትዮጵያውያን ሄደች- ለሙከራ፤ ብዙዎች አላወቋትም።ይህች ፍቅር የሌላት፣ ክርክር የምታበዛ፣ ባህላችንን የማታከብር፣ በሰው ህመም የምትስቅ፣ በሰው ሞት የምትደንስ፣ ይሉኝታ የሌላት፣ የምንናፍቃት ዲሞክራሲ ወይም የሷ መልእክተኛ ልትሆን አትችልም” ብለው አመሳቀሏት።

 አንዳንዶቹ ግን አውቀዋታል፤ አይተው ግን እንዳላዩ መሆን ፈልገዋል።ይህች ባህላችንን ያልጠበቀች ጋጠ ወጥ ስለሆነች በኛ መካከል ምንም ቦታ የላትም” ብለው እያጥላሏት ነው። ሌሎች ደግሞ እሷ እንደሆነች ቢያውቁም፣ኢትዮጵያዊ መልክ ይዛ ካልመጣች፣ እንዳለ በምእራባዊ ልብስ አጊጣ፣ ተገላልጣ፣ እየጮኸች፣ እያወራች ልትገባ አትችልም” ብለው እየተቃወሟት ነው። 

አንዳንዶች ግንምንም ቢሆን ቦታ ሊሰጣት ይገባል፣ ጉልበተኞችን ማክበር፣ ባለጸጎችን ማክበር፣ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ማለት፣ ገና ለገና ባህላችን ነው ተብሎ እንዴት እንታፈን? እንዴት እንገለል?” እያሉ መጮሃቸውን ቀጥለዋል። ከዛም አልፈው  “ሲጀምር ይህ ባህል የምትሉት የጭቆና መሳሪያ እየሆነ እያገለገለ ስለሆነ መፍረስ አለበት” በማለት በቀጥታ ባይሟገቱም በተዘዋዋሪ ለመታገል እየሞከሩ ነው። ደግሞ ሌሎች አሉ፤እስቲ ቀስ በሉ፤ ሁሉንም ቀስ ብለን ማሳካት እንችላለን፤ ነገሮችን በእርጋታ እና በጥንቃቄ እናድርጋቸው፤ ያልሰራናቸውን የቤት ስራዎች ስለፈለግን ብቻ ከሚጠይቀው ጊዜ በፊት ማጠናቀቅ አንችልም፤ ስለፈለግን ብቻ በረን በሰላም እና በብልጽግና ሜዳ ላይ ማረፍ አንችልም። ህዝባችን ህዝባችን ነውና አፈራችንን አራግፈን አፈር ነህ ልንለው አንችልም። የገባን ነገር ካለ እናስረዳው፤ ከሁሉም በፊት ግን በንቀት ሳይሆን በት ህትና እንረዳው፤ ስሜታችንን በአመክንዮ ለማስደገፍ በምናደርገው ጥረት ጊዜአችንን አናባክን፤”  በማለት በመቅለስለስ ይናገራሉ።

“ምንድነው መለማመጥ?” ሌሎቹ የመልሳሉ።የምትቀሰቅሰው የተኛን ሰው ነው እንጅ አውቆ የተኛ የመሰለን አይደለም፤ የምታስተምረው የማይውቅን ሰው ነው እንጅ አውቆ እውቀቱን በስሜት እና በጠባብነት ይጠቅመኛል ለሚለው አላማ የሚያውለውን ሰው አይደለም። ሃዘኔታ እና ርህራሄ የሚያስፈልገው ደካማው ነው፤ ጥንካሬውን መቆጣጠር አቅቶት ደካሞቹን የሚጨፈልቀው አይደለም፤ብለው በጭሆት ይመልሳሉ።

ተቃራኒው ደግሞ ይከተላል፤እውነት አላችሁ፤ እውነት ግን እናንተ ብቻ አይደለም፤ ልትበሳጩ ትችላላችሁ፣ የሚሰሩ ስህተቶች ሊያሳዝኗችሁ ይችላሉ፤ ነገር ግን ያሳዛኞቻችሁን መሳሪያዎች ልትጠቀሙ አትችሉም። አሳዛኞቻችሁ ጥላቻ ስለተጠቀሙ እናንተ ጥላቻ ልትጠቀሙ አትችሉም፤ አሳዛኞቻችሁ መከፋፈል ስለተጠቀሙ እናንተ መከፋፈል  ልትጠቀሙ አትችሉም። እነሱ ሃያ አራት ሰአት ቢያዎሩ ሃያ አራት ሰአት ችላ ሊባሉ ይችላሉ፤ እናንተ ግን ባገኛችሁት ትንሽ እድል እንደ አሳዳጆቻችሁ ከሆናችሁ ፊት የሚዞርባችሁ ይበዛል።”

መሃል ገብቼ የሆነ ነገር ማለት ፈለኩ፤ ተከራከሩ ድንጋይ ግን አትወራወሩ፤ በሃሳብ ተቧቀሱ ጥይት አለመታኮሳችሁን ግን እንደ ትልቅ ድል ውሰዱት።ካልወደድከኝ አትኖራትም፤ከናቅከኝ አታድራትም” ያባቶቻችን ጨዋታ ነው፤ በቃ በሃሳብ ስለተለያየን፣ ከባህላችን ውጭ የሆነ ነገር ሰለተነጋገርን ኢትዮጵያ አለቀላት ልንል አይገባም፤ ኢትዮጵያ በሽዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በጅማላ ሲገደሉባትም አላለቀላትም፤ እናቶች ለተገደሉ ልጆቻቸው ያላቸውን እንባ አፍነው የጥይት ዋጋ ሲከፍሉም አላለቀላትም፤ አንድ እናት አራት ልጆቿን ምንነቱ ለማይገባት የርእዮተ አለም ልዩነት በአንድ ጀንበር ስታጣም አላለቀላትም፤ ሚሊዎኖች ሆነን በርሃብ ስናልቅ፣ መንግስቶቻችን ችላ ሲሉንም አላለቀላትም። ይህን የምለው አንዳንድ ሰዎች የሚሉትን በቅንነት ከልባቸው እንደሚሉ በመረዳት ነው። ከዚያ ውጭ ግን አውቆ የተኛን ለመቀስቀስ አልፈልግም፤ አልተኛማ።